1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደራሲዉ ስራዎች ለስነ-ጥበብ አፍቃሪዎች

ሐሙስ፣ ኅዳር 21 2004

በብሪታንያ በለንደን ከተማ የሚገኘዉ የኢትዮጽያዉያን የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ማህበር እዉቁ የቅኔ፣ የግጥም፣ የተዉኔት ሰዉ የደራሲ ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ በብዕር ስሙ የጎሞራዉ የስነ-ጽሁፍ ቀን በሚል ከተለያዪ የአዉሮጳ አገራት የተሰባሰቡ ኢትዮጽያዉያን ጻህፍትና የኪነ-ጥበብ ሰዎች በተገኙበት የደራሲዉ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች በንባብ መልክ አቅርቦአል።

https://p.dw.com/p/RyiH
ምስል picture alliance/dpa

ከተመሰረተ አንድ አመት የሆነዉ በብሪታንያ የሚገኘዉ የኢትዮጽያዉያን ኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ማህበር በኢትዮጽያ በኪነ-ጥበብ እና ስነ-ጽሁፍ ዘርፍ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ዜጎች ለማሰብ እንደ ተቋቋመ የነገሩን በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በትያትር ኪነ-ጥበብ ሞያ የተመረቁ እና በድርሰት በትወና እና በአስተዳደር ስራ ረዘም ላለ ግዜ ያገለገሉት አቶ በሃይሉ ነቃ-ጥበብ ጋር ዉይይት አድርገናል። ከተለያዩ አዉሮጳ አገራት የመጡ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ስለ ደራሲ ሃይሉ ገብረ ዮሃንስና ስራዉ ያላቸዉን አስተያየት ሰጥተዉናል ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ