የዩጋንዳ ምርጫ
ሐሙስ፣ የካቲት 3 2008ማስታወቂያ
የቀድሞዉ የዩጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን ዳዳ በሐገሪቱ ለሚደረገዉ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ማድመቂያ ሆነዋል።ለፕሬዝደንትነት ከሚወዳደሩት ፖለቲከኞች አንዱ አማም ምባባዚ ከተመረጡ በስደት የሞቱትን የኢዲ አሚንን አስከሬን ወደ ዩጋንዳ ለማስመጣት እና ቤተ-መዘክር ለመሰየም ቃል ገብተዋል።በመጪዉ ሳምንት በሚደረገዉ ምርጫ የተፎካካሪዎች አብይ ርዕሥ የሆነዉ ግን የሥራ አጥነት ፤ የመሠረተ-ልማት አዉታር እና ሙስና ናቸዉ።የናይሮቢዉ ወኪላችን ፋሲል ግርማ እንደተከታተለዉ በምርጫዉ ሐገሪቱን ለሠላሳ ዓመት የገዙት ዩሬ ሙሴቬኒ መሸነፋቸዉ አጠራጣሪ ነዉ።ፋሲል በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ