የዩክሬይን ውዝግብ እና ሩስያ ያቀረበችው ሀሳብ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 30 2006ማስታወቂያ
በዶንትሴክ እና በሉሀንስክ ግዛቶች የሚኖሩ ሦስት ሚልዮን የሩስያ ቋንቋ ተናጋሪዎች የፊታችን እሁድ እንዲያካሄዱት ያቀዱትን ውሳኔ ሕዝብ ወደሌላ ጊዜ እንዲገፉት፣ ከዚሁ ጎንም ምዕራቡ ዓለም ለዩክሬይን ውዝግብ መፍትሔ በሚያፈላልግ የወደፊት ድርድር ላይ በመንግሥቱ አንፃር የሚዋጉትን ሚሊሺያዎችንም እንዲያሳትፍ ሲጠይቁ ተሰምተዋል። የዩክሬይን ፕሬዚደንታዊ ምርጫም ፣ ከምርጫው በኋላ የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች መብት እስከተከበረ ድረስ እንደ አንድ ትክክለኛ ርምጃ ሊታይ እንደሚችል ጠቁመዋል። እርግጥ፣ ውሳኔ ሕዝቡን በተመለከተ ሩስያዊው ፕሬዚደንት ያቀረቡትን ሀሳብ የዩክሬይን የሽግግር መንግሥትም ሆነ መፍቀሬ ሩስያ ኃይላት አልተቀበሉትም።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ