የዩኤስ ፕሬዚደንታዊ እጩዎች ምርጫ በአዮዋ ግዛት
ማክሰኞ፣ ጥር 24 2008ማስታወቂያ
በዚሁ ከዩኤስ አሜሪካ ግዛቶች ሁሉ ቀድሞ የመጀመሪያውን ምርጫ ባካሄደው ግዛት ውስጥ ከሬፓብሊካውያኑ ፓርቲ የቴክሳሱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ ቴድ ክሩዝ ሲያሸንፉ፣ ያሸነፋሉ ተብለው ተገምተው የነበሩት ቢልዮኔሩ ባለተቋም ዶናልድ ትራምፕ ሳይቀናቸው ቀርተዋል። ከዴሞክራቶቹ ፓርቲ እጩዎች ደግሞ የቀድሞ የዩኤስ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን ጠንካራ ተፎካካሪያቸውን የቬርሞንትየሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ በርኒ ሳንደርስን በጠባብ የድምፅ ብልጫ ማሸነፋቸው ተገልጾዋል።
ናትናኤል ወልዴ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ