የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ክርክር
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2005ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ትናንት ማታ ባደረጉት ሰወስተኛና የመጨረሻ የፊት ለፊት ክርክር በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸዉን ሚት ሮምኒን በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸዉ ተመሠከረ።በአብዛኛዉ በዩናይትድ ስቴትስ የዉጪ መርሕ ላይ ባተኮረዉ ክርክር ፕሬዝዳት ኦባማ የአራት አመት የመሪነት ልምዳቸዉን በትክክል ማንፀባረቅ መቻላቸዉን ክርክሩን የተከታተሉ ታዛቢዎች አረጋግጠዉላቸዋል።አገረ-ገዢ ሚት ሮምኒ በበኩላቸዉ ወትሮ ከነበራቸዉ የቀኝ አክራሪ አቋም ተለሳልሰዉ ባንዳድ ጉዳዮች የኦባማ መስተዳድርን መርሕ እስከ መደገፍ ደርሰዋል።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ