1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ክርክር

ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001

ባብዛኛዉ በምጣኔ ሐብት ላይ ባተኮረዉ ክርክር ኦባማ ከመኬይን የተሻለ ነጥብ አግኝተዋል

https://p.dw.com/p/FbL2
ኦባማና መኬይንምስል AP

ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በያዝነዉ ወር ማብቂያ ለሚደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚፎከከሩት የሐገሪቱ ሁለት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እጩዎች ትናንት የመጨረሻዉን የፊት ለፊት ክርርክር አድርገዋል።በሥልጣን ላይ ያለዉ የሪፐብሊካኖቹ ፓርቲ እጩ ሴናተር መኬይንና የተቃዋሚዉ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሴናተር ባራክ ኦባማ ለሰወስተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት ክርክር ከቀዳሚዎቹ ሁለቱ ብዙ የተሟሟቀና አንዱ ሌላዉን በጠንካራ ቃላት የተቸበት ነዉ።ባብዛኛዉ በምጣኔ ሐብት ላይ ባተኮረዉ ክርክር ኦባማ ከመኬይን የተሻለ ነጥብ አግኝተዋል።ነጋሽ መሐመድ የዜና መልዕክቶችን አሰባስቧል።