1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

   የዩናይትድ ስቴትስ ፀረ-ሽብር ዘመቻ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 7 2009

ዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ ካወጀችበት ከ1993 ጀምሮ የአሜሪካ ጦር በገባበት ሐገር በሙሉ በሽብር፤ ጦርነት እና ሁከት እየተተራመሱ ነዉ። አንድ የሶማሊያ ምሁር እንደሚሉት ደግሞ የአሜሪካ ሶማሊያ ላይ የከፈተችዉ ጦርነት ለሐገሪቱ ሕዝብ ያተረፈዉ ሞት እና ስደት ነዉ

https://p.dw.com/p/2UPhh
USA Präsident Obama besucht MacDill Air Force Base
ምስል Reuters/K. Lamarque

MMT/US-War on Terror (Beri.WDC) - MP3-Stereo

ዩናይትድ ስቴትስ የከፈተችዉ ዓለም አቀፍ-ፀረ ሽብር ዘመቻ ጥሩ ዉጤት ማምጣቱን የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር አስታወቀ። መስተዳድሩ ባወጣዉ ባለ-ሥልሳ ገፅ ዘገባ እንዳስታወቀዉ በተለይ በኦባማ ዘመን የተደረገዉ ዘመቻ በአሜሪካ እግረኛ ጦር ላይ የነበረዉን ጫና እና ወጪ የቆጠበ ነዉ። ኦባማም እርምጃቸዉን አወድሰዋል። ይሁንና ዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ ካወጀችበት ከ1993 ጀምሮ የአሜሪካ ጦር በገባበት ሐገር በሙሉ በሽብር፤ ጦርነት እና ሁከት እየተተራመሱ ነዉ። አንድ የሶማሊያ ምሁር እንደሚሉት ደግሞ የአሜሪካ ሶማሊያ ላይ የከፈተችዉ ጦርነት ለሐገሪቱ ሕዝብ ያተረፈዉ ሞት እና ስደት ነዉ። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ