የዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ጊዜ የምርጫ ፉክክር
ሰኞ፣ ጥቅምት 24 2007ማስታወቂያ
በዚሁ መሠረትም በሚካሄደዉ የተወካዮች ምክር ቤትና የሴኔት የማሟያ ምርጫ ሪፐብሊካኖች የላይኛን ምክር ቤት እንደሚረከቡ ይጠበቃል። በተለይም በርካታ ድምፅ ይገኝባቸዋል ከሚባሉ ግዛቶች የተሰበሰበዉ የሕዝብ አስተያየት መመዘኛ ቀመር ሚዛኑ ለሪፐብሊካን ያጋደለ መሆኑን አመላክቷል። ዴሞክራቶች በሴኔቱ ያላቸዉን የበላይነት ለማስጠበቅ ያደረጉት ጥረት በድል የመጠናቀቁ ነገር አጠራጣሪ እንደሆነ ነዉ የሚገመተዉ። ምርጫዉ ሪፐብሊካኖች አላላዉስ ባሏቸዉ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ፖሊሲዎችና ቀጣይ አጀንዳዎች ላይ የሚኖረዉ አንድምታ ምን ይሆን? የዕለቱን የማኅደረ ዜና ጥንቅር ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ