የዩናይትድ ስቴትስ በረዶ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 30 2006ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ፥ በአብዛኛ ግዛቶቿ አዉሮፕላኖች አይበሩም።አዉቶቡሶች አይሸከረከሩም።ትምሕርት ቤቶች አያስተምሩም።ሥራም ባብዛኛዉ የለም።አዉሮፕላን ማረፊያዎች፥ አዉራ-መንገዶች፥ የትምሕርት ቤቶች ሜዳዎች አንድ ነገር ተከምሮባቸዋል።በረዶ።ቅዝቃዜዉ ያዩ እንዳሉት አጥንት ይሰብራል-የሚባል ዓይነት ብቻ አይደለም፥ የአንዳድ ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚሉት ብርድና በረዶዉ ብረቶችን ከማቀዝቀዝ አልፎ-እንደ እሳት ይፋጃል።እስካሁን አስራ-ስድስት ሞቷል።የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ