1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ጉባኤ ፍጻሜ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2006

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው በንግድ በመልካም አስተዳደርና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1CqoS
USA-Afrika-Gipfel in Washington
ምስል Reuters

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰላም አሰከባሪ ኃይል ማቋቋሚያ 110 ሚሊዮን ዶላር ለመመደብ ማቀዷን አስታወቀች ።ትናንት በተጠናቀቀው የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው ሃገራቱ ደፈጣ ተዋጊዎችንና ሌሎች ችግሮችን እንዲቋቋሙ እገዛ ያደርጋል የተባለውን ይህንኑ ኃይል ለመመስረት የሚውለውን ገንዘብ ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው በሚቀጥሉት ሶሶት ዓመታት ነው ።በዚሁ ፈጥኖ ደራሽ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት የአፍሪቃ አገራት ይካተታሉ ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው በንግድ በመልካም አስተዳደርና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።

አበበ ፈለቀ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ