1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩሮ ቀውስና የአውሮፓ መሪዎች ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2004

ግሪክን የመሳሰሉ የዩሮ ተጠቃሚ አገራትን ከዕዳ ቀውስ ማውጣትና ዩሮን በዘላቂነት ማረጋጋት የሚቻልበትን መፍትሄ ለማፈላለግ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች የጀመሩት ጥረት መቋጫ አላገኘም ።

https://p.dw.com/p/RswB
ምስል fotolia/HLPhoto

የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት በገጠማቸው ከባድ ፈተና ላይ መሪዎቹ ባላፈው እሁድ የጀመሩት ውይይት ነገም ይቀጥላል ። በግሪክ ጀምሮ ወደ ሌሌችም የዩሮ ተጠቃሚ አገራት ቀስ በቀስ ለተዛመተው የዕዳ ቀውስ እንዲሁም የጋራውን መገበያያ ገንዘብ ዩሮን ለማረጋጋት በቀረቡት የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ በአውሮፓ ህብረት በየደረጃው ምክክር ሲደረግ ና የመፍትሄ ሃሳቦችም ሲቀርቡ ብዙ ወራት አልፈዋል ። ባለፈው እሁድ የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ከነዚህ ሁሉ የላቀውና ከፍተኛ ትኩረትም የተሰጠው አብይ ጉባኤ ነበር ። በእሁዱ ጉባኤ ላይ የግሪክ የዕዳ ቅነሳ ፣ የአውሮፓ ባንኮችን ከክስረት ለማዳን የቀረበው እቅድ እንዲሁም ለአውሮፓ የገንዘብ ማረጋጊያ ስርዓት መርሃ ግብር የሚመደበው የመጠባበቂያ ገንዘብ መጠን ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ ሳይደረስባቸው ለነገ የተገፉ ሶሶቱ አብይ ጉዳዮች ናቸው ። መሪዎቹ በነዚህ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ነገ ረቡዕ እንደገና በመምከር ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ