የዩሮ ቀዉስና የአዉሮጳ አገሮች
ዓርብ፣ ኅዳር 15 2004ማስታወቂያ
የጋራ መግባባትን ለመፍጠርም ትናንት ፈረንሳይ ሽትራስቡርግ ዉስጥ በሚገኘዉ የአዉሮጳ ኅብረት ምክር ቤት የጀርመን፤ ፈረንሳይ መሪዎች አዲስ ከተመረጡት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ሞንቲ ጋ ተወያይተዋል። እንዲያም ሆኖ ፈረንሳይና ጀርመን የአዉሮጳ ማዕከላዊ ባንክ ለቀዉሱ መፍትሄ ለመፍጠር በሚኖረዉ ሚና ላይ መከራከራቸዉ ተሰምቷል። ፈረንሳይና ጀርመንን ያላግባባዉ ነጥብ የቲ ነዉ፤ የዩሮ ዞን ቀዉሱንስ ለመፍታት የአዉሮጳ ማዕከላዊ ባንክ ሊኖረዉ የሚችለዉ ድርሻ ምን ይመስላል፤ የሚሉትንና ተያያዥ ጥያቄዎች በማንሳት የብራስልሱ ወኪላችንን ገበያዉ ንጉሤን በጉዳዩ ላይ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሠ