የየመን የክብር ዘብ ጥቃት
ዓርብ፣ ነሐሴ 11 2004ማስታወቂያ
የየመን የክብር ዘብ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሃገሪቱን የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከቦ የሰነዘረው ጥቃት የመንን ለማረጋጋት የሚደረገውን ጥረት እንዳያደናቅፍ እያሰጋ ነው ። አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ከጥቃቱ በስተጀርባ የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳልህ አሉበት ይላሉ ። በልጃቸው በጀነራል አህመድ አሊ አብደላ ሳልህ የተመራው ና በከባድ መሣሪዎች የታገዘው ይኽው ጥቃት የተፈፀመው አዲሱ የየመን ፕሬዚደንት አብዱራባህ ማንሱር ሃዲ የየመን ጦር ኃይል የመዋቅር ለውጥ እንደካሄድ ባዘዙ በሳምንቱ ነው ። ለውጡ የጀነራል አህመድን ሥልጣን ይቀንሳል ። ዝርዝሩን ነበዩ ሲራክ ከጅዳ ልኮልናል።
ነበዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ