የየመን ወቅታዊ ሁኔታና ኢትዮጵያውያን
ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2007ማስታወቂያ
ቁስለኞቹ ሀረድ በሚባል ቦታ አንድ ሐኪም ቤት እንደሚገኙም የየመኑ ወኪላችን ጠቅሷል። በሣዑዲ ዐረቢያ አዝማችነት በአየር የተከፈተው ጥቃት ዛሬ የአማጺያኑን ሚሳይሎችን እና የጦር መሣሪያ ማከማቻ መጋዘኖችን እንዳወደመ፣ ማስራቅ በተባለው ቦታ ከ40 በላይ ስደተኞች መገደላቸውን ደግሞ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የተገደሉት ሰዎች የየትኛው ሀገር ዜጎች እንደሆኑ ግን የዜና ምንጮቹ አልጠቀሱም አልጠቀሱም። የየመኑ ወኪላችን ግሩም ተክለሐይማኖትን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር። በየመን ዛሬ ጦርነቱ ምን መልክ እንዳለው በመግለጥ ይጀምራል።
ግሩም ተክለሃይማኖት
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ