የዞን ዘጠኝ ፀሐፍት
ዓርብ፣ ጥር 19 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዞን ዘጠኝ የድረ ገጽ ፀሀፍት በቀረበባቸው አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት የያዘውን ቀጠሮ እንደገና አራዘመ ። ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት መስሪያ ቤት የተላከ ሲዲ እና ሌሎች ሰነዶች ተፈልገው እንደተገኙ እና እየተመረመሩም መሆኑን በመግለፅ ሌላ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ