የዝቋላ ተራራ አካባቢ ደን ቃጠሎ 12 መጋቢት 2004ረቡዕ፣ መጋቢት 12 2004በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙርያ ባለው ደን የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ሲጠፋ ሲነሳ አሁንም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ይገኛል። ቅዳሜ መጋቢት ስምንት ቀን ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ አዱላበ ከሚባለውhttps://p.dw.com/p/14OnVማስታወቂያ ከገዳሙ ደቡባዊ ምሥራቅ አቅጣጫ የተነሳው የደኑ ቃጠሎ በመነኮሳቱና ባካባቢው ምዕመናን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ቃጠሎው እስከትናንት አመሻሽ ድረስ ዘልቋል። ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ የገዳሙ ባለቤትና ጠባቂ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ችግሩ እንዲወገድ አስፈላጊውን ርዳታ አላፈላለገም በሚል ምዕመናኑ ወቀሳ ሰንዝረዋል። ታደሰ እንግዳው አርያም ተክሌ ሒሩት መለሰ