የዛፎች እናት" ዋንጋሪ ማታይ"
ማክሰኞ፣ መስከረም 16 2004ማስታወቂያ
« ልክ እንደኔ ከአዳጊ አገሮች ከተመጣ- መቼም አንድ ቀን ከመሞቴ በፊት አዳጊ የሚለውን ቃል መጠቀም አቆማለሁ ብዬ አስባለሁ!! ምክንያቱም እስከመቼ እንደምናድግ አላውቅምና! » አሉ አገራቸው ኬኒያ ከአደጉት አገራት ጎን ተሰልፋ ለማየት ሳይበቁ ማታይ ሞት ቀደማቸው። ያለፈው እሁድ በናይሮቢ ሆስቲታል ባደረባቸው የማህፀን ካንሰር ህይወታቸው አለፈች። ይሁንና ማታይ በዚች አለም እስከነበሩ ድረስ በርካታ አስተዋፅዎ ለአገራቸው ከዛም ተርፎ ለአፍሪቃ አስተዋፅዎ አድርገዋል። «ማማ ሚቲ» እያሉ ነው ኬንያውያን እኚን እውቅ ወይዘሮን ይጠሩዋቸው የነበረው። ማይታ በኬኒያ እና በሌሎች 13 የአፍሪቃ አገሮች ደኞች እንዳይጨፈጨፉ ጥረዋል። ልደት አበበ