የዛምቢያ ፕሬዚደንት ሥርዓተ ቀብር
ማክሰኞ፣ ኅዳር 2 2007ማስታወቂያ
በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከተሳተፉት መሪዎች መካከል የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚደንት ኬኔት ካውንዳ፣ የዚምባብዌ እና የኬንያ ፕሬዚደንቶች ሮበርት ሙጋቤ እና ኡሁሩ ኬንያታ ሲጠቀሱ ፣ የናሚቢያ እና የማዳጋስካር ጠቅላይ ሚንስትሮች እና በርካታ ምክትል ፕሬዚደንቶችም ተገኝተዋል። በዛሬው የቀብር ሥነ ሥርዓት ምክንያት በዛምቢያ ትምህርት ቤቶች፣ መደብሮች እና የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ተዘግተው ውለዋል። ዛምቢያን እአአ ከ2011 ዓም ወዲህ የመሩት የ77 ፕሬዚደንት ማይክል ሳታ እአአ ባለፈው ጥቅምት 28 ነበር ከረጅም ህመም በኋላ ህክምና ያደርጉባት በነበረችው የብሪታንያ መዲና ለንደን ሕይወታቸው ያለፈችው። በዛምቢያ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ አዲስ ፕሬዚደንት እስኪመረጥ ድረስ ትውልደ ስኮትላንድ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንት ጊ ስኮት ሀገሪቱን ይመራሉ።
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ