የዚምባብዌ ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ምስረታ
ሰኞ፣ የካቲት 2 2001ማስታወቂያ
። የዛሬ ዓመት መጋቢት የተካሄደውን የዚምባብዌ የመጀሪያ ዙር ምርጫ ውጤትን ተከትሎ ለወራት ከዘለቀው ብጥብጥና ውዝግብ በኃላ ተቃዋሚው MDC ከሙጋቤ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ጋር ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ለመመስረት የተስማማው በደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማህበረብ SADEC ሸምጋይነት ነው ። እንደ ፖለቲካ ተንታኞች አስተያየት ከሆነ ሳዴክ ሁለቱን ወገኖች በማግባባቱ ሂደት በተለይ በMDC መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ ላይ ከፍተኛ ጫና አድርጓል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ MDC በስደት ዚምባብዌ የሚኖሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያምን ወደ ኢትዮጵያ መመሰል እንደሚፈልግ አስታውቋል ።