1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባቡዌ ተስፋ

ረቡዕ፣ መስከረም 7 2001

ሐራሬ-ዚምባቡዌ።ሥምምነቱ ተፈረመ።።ፀደቀ-ተደነቀም።

https://p.dw.com/p/FJe1
ከግራ ወደ ቀኝ፥-ሙታምበራ፥ ሙጋቤና ችቫንገራይምስል AP
ሥምምነቱ ለዚምባቡዌ ሕዝብ የችግር-ስደት ኑሮዉ ፍፃሜ-መዳረሻ፣ የሰላም፣ ደሕንነቱ ተስፋ ጭላንጭል ለመሆኑ ባለፈዉ ሐሙስ ከሐራሬ እስከ ጁሐንስ በርግ የዉድቅት ፀጥታታን በፌስታ-ፍንደቃ ገፎ ከማደሩ የቀረበ ማረጋጋጪያ የለም።ለታቦ ኢምቤኪ ክብር-ለአፍሪቃዉን መሪዎች በሙሉ ደግሞ የአፍሪቃን ችግር መፍታት የመቻላቸዉ አኩሪ-ምሥክር፣ ለአፍሪቃ ሕዝብ ተስፋ ነዉ።በፖለቲካዉ ቀዉስ የታየዉ ሐቅ የቀዉሱ ምንጭ-ዚምባቡዌ ብቻ፥ አራጋቢ-አቀጣጣዮቹ፥ ፖለቲከኞቿ ብቻ፣አለመሆናቸዉን ማረጋገጡ ግን ርካታ፣ ደስታ፣ ክብር ኩራት ተስፋዉን እንዳያናጋዉ ያሰጋል።