1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዕዳ ምህረት ለዩጋንዳ፧

ሰኞ፣ ሰኔ 20 1997

የበለጹጉት መንግሥታት፧ በቅርቡ እንዳስታወቁት፧ እጅግ ለደኸዩት አገሮች 100% የዕዳ ምኅረት፧ ባጠቃላይም፧ ለ 37 አገሮች፧ 55 ቢልዮን ዶላር ዕዳ ይሰረዝላቸዋል። በዓለም አቀፉ የዕዳ ሥረዛ ነክ የሥራ እንቅሥቃሴ፧ እ ጎ አ በ 1988 ዓ ም፧ የመጀመሪያዋ ተጠቃሚ የሆነችው፧ ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር፧ ዩጋንዳ፧ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ልጆች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ አብቅታለች። ያኔ 3.6 ቢልዮን ዶላር ዕዳ እንደነበረባት ነው የተገለጠው።

https://p.dw.com/p/E0eW
ከ ሰባት ዓመት ወዲህ ደግሞ፧ ዩጋንዳ ከዚያ ታይቶም ተሰምቶም ባልታወቀ ሁኔታ፧ የ 4.9 ቢልዮን ዶላር ዕዳ ተሸካሚ ሆናለች። የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያስረዳው፧ ለትምህርት የተመደበው ገንዘብ ተቀንሶ፧ 13 ከመቶው ብቻ ነው፧ ሥራ ላይ የዋለው።
የኤኮኖሚ ምሁሩና ጋዜጠኛው አንድርው ምዌንዳ፧ ዕድሳት ያላገኙ የካምፕላን የኢንዱስትሪ ማዕከላት፧ ፈንጂ የማሳቸው የመሰሉ ጎዳናዎችን ያረጀውን ሐዲድና በየቦታው የተከመረ ቁሻሻ ከቢሮው ሆኖ በመስኮት ኣሻግሮ ይመለከታል። ከዚያ በስተጀርባ ደግሞ፧ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፧ ባንኮችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጽህፈት ቤቶች ይገኛሉ። ምዌንዳ እንዲህ ይላል።
O-Ton(
«የዕዳ ሥረዛው ድሆችን አይረዳም፥ በአንጻሩ የእኛ አምባገነኖች በእስዊስ በሚገኙ ባንኮች ገንዘብ ማስቀመጫ ሂሳባቸው እንዲሞላ ያደርጉበታል። የጦሩ ኃይሉን ቁጥር ይጨምራሉ። የመንግሥት ሠራተኞችና የፖለቲካ ተጠቃሚዎችም፧ ኪሣቸው በገንዘብ እንዲሞላ ይደረጋል።«
የዩጋንዳ መንግሥት፧ ከ ሰባት ዓመት በፊት የተሃድሶ ለውጥ ለማራመድ፧ ድሕነትን ለመታገል ትምህርት ቤቶችንና ሀኪም ቤቶችን ለመገንባት፧ የገጠሩን መሠረተ-ልማት ለማፋጠን ቃል ቢገባም፧ አልሆነም። ህዝቡ ምንም አላገኘም። ዛሬ፧ ዩጋንዳ ከ ሰባት ዓመት ወዲህ ከምንጊዜውም የበለጠ፧ በአጠቃላይ፧ የ 4.9 ቢልዮን ዶላርዕዳ ተሸካሚ ሆናለች። አሁንም፧ አንድርው ምዌንዳ፧
O-Ton
«መንግሥት 68 ሚንስቴሮች፧ አቋቂሞአል። አዲስ የአስተዳደር አጥቢያዎች መድቦ፧ ፓርላማውንም ልክ አንድ የእግር ኳስ መጫዎቻ ሜዳ አስመስሎ አሥፍቶታል።
የዕዳ ምህረት ወይም ሥረዛ ማለት፧ ገንዘብ ለማባከን፧ ፈቃድ መስጠት ማለት ነው«። የመዘርዝር ጥናት ውጤት እንደሚጠቁመው ዩጋንዳ መለስተኛ ዕድገት ማስመዝገቧ እሙን ነው። የራሷ ማዕድን ባይኖራትም፧ አፍሪቃ ውስጥ፧ ከታወቁት ወርቅና አልማዝ ሻጭ አገሮች መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች። የዩጋንዳ ጦር ጣልቃ በመግባት፧ ተሠማርቶ እንደነበረ አይካድም። የዩጋንዳ መንግሥት፧ በኮንጎ ጣልቃ የገባው ጦሩ የዘረፈውን ሀብት፧ እንደ ካሣ ነው የቆጠረው። የዓለም ባንክም «አበጀህ!« ነው ያለው። የሆነው ሆኖ፧ ዩጋንዳ፧ በገንዘብ አያያዝ፧ በመንግሥት አመራርም ሆነ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ፧ ገና ብዙ ማሻል ይጠበቅባታል ነው የሚባለው።
በአሁኑ ጊዜ፧ የዩጋንዳ መንግሥት ህገ መንግሥቱን ለማሻሻል ነው ጥረት እያደረገ ያለው። 20 ዓመት በሥልጣን የቆዩት ሙሴቬኒ፧ የዕድሜ ልክ ፕሬዚዳንት መሆን የሚችሉበት አንቀጽ ነው ይሻሻላል የተባለው። ጋዜጠኛ አንድርው ምዌንዳ፧
እርዳታ ለጋሽ አገሮች፧ የራሳቸውን የኤኮሚና የፖለቲካ ጥቅም ብቻ ሆኗል፧ የሚመለከቱ በማለት ወቀሣ ሰንዝሯል። የዚህ የራስን ጥቅም ብቻ የመመልከቱ እርምጃ፧ በአፍሪቃውያን ዘንድ ድህነትን፧ ለማኝነትንና በራስ ጉዳይ ኀላፊነት መሸከም አለመቻልን ነው ያስከተለው። ምዌንዳ፧ አስተያየቱን ሲያጠቃልል፧
O-Ton
«የአፍሪቃ የዕዳ ምህረት(ሥረዛ)፧ ወይም ተጨማሪ የልማት ዕርዳታ አያስፈልገውም። ለአፍሪቃ የሚያሻው፧ ገንዘብ፧ በግል፧ ሥራ ላይ የሚውልበት እርምጃና የዓለም ገበያ ክፍት እንዲሆንለት ነው« ብሏል።