የዕዉቀት ልውውጥ፣ አፍሪቃዉያን ጠበብት በጀርመን
ረቡዕ፣ ጥቅምት 6 2006የልምድ ልዉዉጥን አድርጓል። በዕለቱ ዝግጅታችን የቮልክስቫገን ተቋም ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተካፋይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ይዘን ቀርበናል፤
ታዋቂዉን የጀርመን የመኪና ኩባንያ ስምን የያዘዉ «የፎልክስቫገን ተቋም» በሳይንስ፤ በቲክኒክ፤በሕክምና፤ በማህበረሰብ ሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ በሚደረግ የምርምር ሥራን፣ ተቋሙ በተለይ በአፍሪቃ የሚገኙ ምሁራንን እና የምርምር ሥራዎቻቸዉን በመደገፉ የሚታወቅ ተቋም ነዉ። ከአፍሪቃ ብቻ ከስድሳ በላይ ምሁራን እዉቀት በተለዋወጡበት መድረክ ላይ ከተገኙት ኢትዮጵያዉያን መካከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዶክተር ሜሮን ዘለቀ ይገኙበታል፤
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፤ በአንትሮፖሎጂ ማለትም በስነ- ሠብ ጥናት ትምህርት ክፍል፤ መምህር የሆኑት ዶክተር ሜሮን ዘለቀ በዚሁ በጀርመን ሀገር በሚገኝ ከፍተኛ ተቋም ነዉ የዶክትሪት ማዕረጋቸዉን ያገኙት፤ ዶክተር ሜሮን የሳይንስ ምርምርና ጥናት በሀገራችን ከፍተኛ እድገት እያሳየ መምጣቱን ይገልፃሉ፤
ኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ሳይንስ አካዳሚ፤ ዋና ዳይሪክተር ፕሮፊሰር ብርሃኑ አበጋዝ በፎልክስቫገኑ ተቋም ጉባኤ ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት የሳይንስ ምሁራን መካከል አንዱ ነበሩ፤
በአጠቃላይ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከ 150 በላይ ምሁራን የተካፈሉበት ጉባኤ ላይ የወጣት ምሁራን ሚና በሚል ርዕስ ጥናት ማቅረባቸዉን የገለፁልን የአፍሪቃ የሳይንስ አካዳሚ ዳይሪክተር ፕሮፊሰር ብርሃኑ አበጋዝ፤
የፎልክስቫገኑ ተቋም እያደረገ ያለዉ ድጋፍ የሚበረታታ ነዉ ያሉት ፕሮፊሰር ብርሃኑ፤ በተለይ ደግሞ የአፍሪቃ መንግስታት በሳይንሱ ዘርፍ የሚመድቡት በጀት ሊታሰብበት ይገባል፤
እዉቀት ለነገ በሚል መርህ ለ ሁለት ቀናት በተደረገዉ ጉባኤ የተሳተፉት እና ከፎልክስቫገን ተቋም ለምርምር ስራቸው ድጋፍ ያገኙት ዶክተር ሜሮን ዘለቀ በመጨረሻ፤
አፍሪቃዉያን የሳይንስ ምሁራንን ጋር የልምድ ልዉዉጥ ለመፍጠር በሚል በፎልክስቫገን ተቋም በተዘጋጀዉ ጉባኤ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን ለሰጡን ቃለ ምልልስ እናመሰግናለን፤ ሙሉዉን የድምፅ ዘገባ ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ