1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፋሰሱ ሀገራት ጉባኤና ዉጤቱ

ዓርብ፣ ሰኔ 23 2009

የአባይ ተፋሰስ ሀገራት መሪወች ባለፈዉ ሳምንት በዩጋንዳ ኢንተቬ ጉባኤ አካሂደዋል።በጉባኤዉ  ኢትዮጵያ እየገነባች ስላለዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በቀጥታ ባይነሳም  ግብፅ ወደ አባይ የትብብር ማዕቀፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትመለስ ጥሪ መቅረቡን የኢትዮጵያ የዉሃ ፣የመስኖና  የኤለክትሪክ ሚንስቴር ገልጿል።  

https://p.dw.com/p/2fir5
Nil Dammbau in Äthiopien Archiv 28.05.2013
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

Nile Basin Countries Summit - MP3-Stereo


 በጉባኤዉ የኢትጵያ ፣የግብፅ እንዲሁም የጉባኤዉ አስተናጋጅ ሀገር ፤ዩጋንዳ መሪ ዪዌሪ ሞሶቬኒ የተሳተፉ ሲሆን ሌሎቹ የተፋሰሱ ሀገራትም  ተወካዮቻቸዉን ልከዋል።    የኢትዮጵያ የዉሃ የመስኖና  የኤለክትሪክ ሚኒስቴር ከጉባኤዉ መጠናቀቅ በኋላ ሰኔ 20 ቀን 2009  በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የሁለቱ ሀገራት መሪወች  ተገናንተዉ መወያየታቸዉ  አወንታዊ ርምጃ ነዉ ሲል ገልጿል።በዉይይቱ ሀገራቱ በጋራ ስለሚሰሩባቸዉ የግብርና ፣የኤለክትሪክ እንዲሁም የንግድና የኢንቨስትመንትና ጉዳዮች  ትኩረት የተሰጣቸዉ  መሆናቸዉን በሚኒስቴር  መስሪያ ቤቱ  የኮምኒኬሽንና  የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ  ወይዘሮ አስቴር ተክሌ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

ስለ አባይ ተፋሰስ ሀገራት በተለይም ስለ ኢትዮጵያና ግብፅ ሲነሳ ተያይዞ የሚነሳዉ ካለፉት ስድስት አመታት ጀምሮ ኢትዮጵያ እየገነባችዉ ያለዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ነዉ።የሀገሪቱ መንግስት ግድቡ በታችኛዉ የተፋሰሱ ሀገራት የሚያመጣዉ ተፅዕኖ እንደሌለ በተደጋጋሚ ቢገልፅም በሀገራቱ መካከል አሁንም ድረስ በቂ  መተማመን ላይ አልተደረሰም።ያም ሆኖ ግን የኢንተቬዉ የተፋሰሱ ሀገራት የመሪወች ጉባኤ ጉዳዩን ለዉይይት አላቀረበዉም።የመረጠዉ በሌሎች አጀንዳወች መወያየትን ነዉ።

ኢትዮጵያና ግብፅ በጋራ ስምምነት የግድቡን ተፅዕኖ የሚያጠኑ ሁለት ድርጅቶን መርጠዉ ወደ ስራ መስገባታቸዉ ሲገለጽ ቆይቷል።ይሁን እንጅ ከጉባኤዉ መጠናቀቅ በኋላ በተሰጠ መግለጫ ፤የግድቡን የዉሃ ሙሌት ስራ ለመጀመር ኢትዮጵያ የጥናት ዉጤቱን እንደማትጠብቅ  መገለጹ እያነጋገረ ነዉ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ

Äthiopien Grand Renaissance Staudamm al-Sisi al-Bashir Desalegn
ምስል Ashraf Shazly/AFP/Getty Images

«ከጥናቱ ጎን ለጎን የግድቡ ስራ ይቀጥላል» ካሉ በኋላ ግድቡን በዉሃ የሞሙላት ስራም ቢሆን« የጥናቱን ዉጤት እስከሚጠናቀቅ  ቆመን አንጠብቅም » ሲሉ አመልክተዋል።

በዉይይቱ በቀጥታ የግድቡ ጉዳይ ባይነሳም ሀገራቱ የናይል ትብብር ማዕቀፍን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ መክረዋል ተብሏል። ትብብሩን  ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ በተለይ ግብፅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቀድሞ አባል ወደ ነበረችበት የትብብር ማዕቀፍ እንድትመለስ ጥሪ ቀርቦላታል ሲሉ ም/ዳይሬክተሯ አመልክዋል።የናይል ቤዚን ኮሚሽን እንዲቋቋምም ሀሳብ መቅረቡም ከምንስቴር መስሪያቤቱ የተገኜዉ መረጃ ያሳያል።

ሙሉዉን ዘገባ የድምፅ ማዕቀፉን  በመጫን ያዳምጡ።

ፀሐይ ጫኔ 

አርያም ተክሌ