1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የዉሃ ሳምንት ማጠናቀቂያ

ዓርብ፣ ነሐሴ 20 2003

በስዊድን ስቶክሆልም ካለፈዉ እሁድ አንስቶ ሲካሄድ የቆየዉ የዓለም የዉሃ ሳምንት ጉባኤ እስከመጪዉ የአዉሮጳዉያን 2030ዓ,ም ድረስ ሊደረግ ይገባል ያላቸዉን ነጥቦች በማመልከት ዛሬ መግለጫ አዉጥቷል።

https://p.dw.com/p/RiOn
ምስል Fotolia/Udo Kroener

በጉባኤዉ የተሳተፉ አንድ የተመድ ባለስልጣን በዓመት 198 ቢሊዮን ዶላር ቢመደብ ቢያንስ ለግማሽ ቢሊዮን ህዝብ ያልተቋረጠ የንፁህ ዉሃ አቅርቦት ማዳረስ እንደሚቻል ተናግረዋል። ይህም በንፁህ የመጠጥ ዉሃና የንፅህና መጠበቂያ ስልት እጦት ለከባድ በሽታዎች ብሎም የሞት አደጋ የሚጋለጠዉን ህዝብ ቁጥር መቀነስ ያስችላል። መግለጫዉን የተመለከተዉን የስቶክሆልም ወኪላችን ቴዎድሮስ ምህረቱን ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብዬ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤ በጉባኤዉ ላይ ከሁለት ሺህ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች መሳተፋቸዉ፤ ከእነሱ መካከለም ኢትዮጵያዉያን ባለሙያዎች እንደሚገኙበት ቴዎድሮስ ገልፆልናል፤ ጉባኤዉ ነገ ጠዋት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ቴዎድሮስ ምህረቱ

ሸዋዬ ለገሰ

ነጋሽ መሐመድ