የዓለም የኤድስ ቀን በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2003ማስታወቂያ
የዛሬ 27 ዓመት HIV መኖሩ በታወቀበት በኢትዮጵያም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኙበት አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ በልዩ ልዩ ከተሞች ዕለቱ ታስቧል ። የአዲስ አባባውን ስነ ስርዓት ታደሰ እንግዳው ተከታትሏል ። ወደ አዲስ አበባው የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረትና የማርያም ፀበል መጠመቂያዎች ብቅ ብሎም ከ HIV በፀበል ለመፈወስ የሚጠመቁ በፀበል ተፈውሰናል የሚሉ እና የፀበሉን ስፍራ ሀላፊ አነጋግሯል ። ወኪላችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ደግሞ ከ HIV ጋር የምትኖረውን የድሬዳዋን ወይዘሮ ፍሬ ህይወት ታደሰን አነጋግሮ ዘገባ አጠናቅሯል ።
ታደሰ እንግዳው ፣ ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ፣
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ