1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የኤኮኖሚ ተስፋ በ2015

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 2007

ከትናንት በስተያ በተሰናበትነው እጎአ በ2014 ፣ዓለም በተለያዩ ጂኦ ፖለቲካዊ ቀውሶችና በወረርሽኝ ብትጠቃም ኤኮኖሚዋ ግን በ3 በመቶ ከማደግ አልተገታም ። ሐሙስ አንድ ባልነው በ2015ስ ምን ይጠበቅ ይሆን ?

https://p.dw.com/p/1EEMI
ምስል imago/Birgit Koch

አዲስ የገንዘብ ቀውስ ? ወይስ ምናልባት የቻይና ክስረት ስጋት ? ቀጣዩ የዶቼቬለው ዛንግ ዳንሆንግ ዘገባ የዓለም ኤኮኖሚ በ2015 ምን ገጽታ ሊኖረው እንደሚችል ያስቃኘናል ።ትናንት በባተው በ2015 የዩሮ ቀጣና እንደገና የዓለም ዋነኛ የኤኮኖሚ ችግር ሆኖ መዝለቁ አይቀርም እንደ ዳንሆንግ ዘገባ ። በጋራው ሸርፍ ዩሮ በሚገበያዩ ሃገራት የሚጠበቀው እድገት አነስተኛ እንደሚሆነ ነው የተገመተው ።በጀርመን ማዕከላዊ ባንክ ዋና የኤኮኖሚ ባለሞያ ሽቴፋን ቢልማየር

«በ2015 በዩሮ ቀጣና 0.8 በመቶ የኤኮኖሚ እድገት ብቻ ነው የምንጠብቀው»

በአንዳንድ የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ውስጥ ያሉ ችግሮች አሁንም ተንታኞችን እንዳሰጉ ነው ።በተለይም ግዙፍ ኤኮኖሚ በሚያንቀሳቅሱት አንዳንድ የሸርፉ ተጠቃሚ ሃገራት ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ይላሉ መቀመጫውን ኤሰን ጀርመን ያደረገው በምህፃሩ RWI የተባለው ተቋም ባልደረባ ሮላንድ ዶህርን ። በአንፃሩ ይላሉ በአንዳንድ ሃገራት ደግሞ ለውጭእየታየ ነው ።

«ለምሳሌ በኢጣልያ ያለው ሁኔታ እጅግ ተለዋዋጭ ነው ።የኤኮኖሚው እንቅስቃሴ ዝግመት ቀጥሏል ።ሆኖም በፈረንሳይ መንግሥት ተጨማሪ ገንዘብ በማውጣቱ ችግሮቹ ተቃለዋል።»

Symbolbild Exporten aus China
ምስል picture-alliance/dpa

ከአቅም በታች የሚንቀሳቀሱ የዩሮ ቀጣና አባል ሃገራት በጀርመን የኤኮኖሚ እድገት ላይ ተፅእኖ ሊያያሳድሩ እንደሚችሉ ነው የሚገመተው ። አብዛኛዎቹ የጀርመን የውጭ ንግድ ደንበኞች ናቸውና ።የጀርመን ፌደራል ባንክ እንዳስታወቀው የጀርመን የሃገር ውስጥ ምርት የተጣራ ገቢ በ2015 በ1 በመቶ ብቻ ያድጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።የጀርመንን የኤኮኖሚ እድገት በ2015 እንዲቀንስ ያደርጉታል ተብሎ ከሚታመኑት ምክንያቶች ውስጥ እንደ ዶህርን አስተያየት አንዱ ተጨማሪ የኤኮኖሚ ማሻሻያዎች እርምጃዎች ተግባራዊ አለመሆናቸው ነው ። ዶህርን መንግሥት ለማህበራዊ ጉዳዮች የሚያወጣውን ገንዘብ ከፍ ከማድረጉ ጋር የተሃድሶ እርምጃዎችን ባለመውሰዱ ይተቻሉ ። በተለይ ዶህርን አጥብቀው የሚነቅፉት በጀርመን የጡረታ መውጫ እድሜ ወደ 67 ከፍ የሚያደርገውን አወዛጋቢውን አዲስ ህግ ነው ።

«ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው ገንዘብ ኩባንያዎችና ለጡረታ መዋጮ የሚያደርጉ አካላት ናቸው የሚሸፍኑት።ይህ ደግሞ ለድርጅቶች ትልቅ ጫና ነው ። የተጠቃሚው የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ያደርጋል ።»

ከዓለም በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኤኮኖሚ የምታንቀሳቅሰው ቻይና በዓመቱ 7 ከመቶና ከዚያም በላይ እድገት ታስመዘግባለች ተብሎ ይጠበቃል። ቻይና የሚገጥሟትን ፈተናዎች ሁሉ ትቋቋማለች የሚል እምነትም አለ ።

ዳንሆንግ ዛንግ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ