1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የሰብዓዊነት ቀን

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 13 2006

በግጭት ጦርነት እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የተሠማሩ ወገኖች ተግባር ማለትም ሰብዓዊነት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነዉ ዛሬ። ለሰብዓዊ ተግባራት ተሠማርተዉ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋልጠዉ ህይወታቸዉን የሚያጡ ወገኖች ዛሬ ዛሬ ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Cx6E
Afghanistan Humanitäre Hilfe aus Deutschland ARCHIVBILD 2005
ምስል picture-alliance/AP Photo

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ሠራተኞች ላይ የሚደርሰዉ ጥቃት ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2012ዓ,ም ወዲህ ብቻ በ66 በመቶ ከፍ ብሏል። የእርዳታ ሠራተኞችን ደህንነት የሚመለከተዉ ዘገባ ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ብቻ 155 የእርዳታ ሠራተኞች መገደላቸዉን፤ 171 ደግሞ በከባድ ሁኔታ መቁሰላቸዉን ያመለክታል። 132ም ታግተዋል። ዘንድሮም ከጥር ወር እስከ ነሐሴ ድረስ የተገደሉት 79 ደርሰዋል። በተለይም በዚሁ ወር ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ስድስት እስራኤል ጋዛ ዉስጥ 11 የእርዳታ ሠራተኞች መገደላቸዉ ተመዝግቧል። አፍጋኒስታን የእርዳታ ሠራተኞች ከየትኛዉም ሀገር በበለጠ ለከፍተኛ አደጋ የሚጋለጡባት ተብላለች። የዓለም የሰብዓዊነት ቀን አዲስ አበባ ላይ ታስቦ ነዉ የዋለዉ፤ ስለተከናወኑ ነገሮች እንዲያጋራን በስፍራዉ የተገኘዉን ዘጋቢያችንን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ