1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የምጣኔ ሃብት ቀዉስና አፍሪቃ

ሰኞ፣ ግንቦት 3 2001

በዓለም የተከሰተዉ የምጣኔ ሃብት ቀዉስ በምድራችን በየስፍራዉ በተለይም በአፍሪቃ የተባባሰዉን ዉጥረት ሊያፈነዳዉ እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ትብብርና የልማት ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃሩ OECD ዛሬ አስጠነቀቀ።

https://p.dw.com/p/Ho2N

ይህን ተቋም ጨምሮ የአፍሪቃ የልማት ባንክና የተመ የአፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ኮሚሽን በጋራ እንዳመለከቱትም የአህጉሪቱ የልማት እድገት ባለፈዉ ዓመት ከታየዉ ዘንድሮ እጅግ ሊቀንስ ይችላል። ከዚህ በመነሳትም በፋይናንስ ቀዉስና ክስረት የተመቱ ኩባንያዎቻቸዉ እንዲያገግሙ በሚያደርጉት ጥረት ቀልባቸዉ የተያዘዉ ለጋሽ አገራት ለአፍሪቃ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳያስተጓጉሉ OECD አበክሮ ጠይቋል።

AFP-ZPR/AA

ሸዋዬ ለገሠ/