1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባኤ በሮም

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2003

በርካታ የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት ተወካዮች የተሳተፉበት የዓለም የምግብ ዋስትና ኮሚቴ ጉባኤ ሮም ኢጣልያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው ።

https://p.dw.com/p/PdcD
ምስል AP

ከትናንት በሰተያ ሰኞ ተጀምሮ አርብ የሚያበቃው ይኽው ጉባኤ በተለይ በምግብ ዋጋ ንረትና በ መሬት ሽምያ ምክንያት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው የምግብ ዋስትና ሁኔታ ይመረምራል ። የዓለም የምግብ ና የእርሻ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር FAO ሩስያ ስንዴን የመሳሰሉ ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርብ በማገዷ የምግብ ዋጋ ቢንርም ዘንድሮ በዓለም ዙሪያ የተሻለ ምርት ስለተገኘ እጎአ በ2007 - 2008 የደረሰው ዓይነት የምግብ ዕጥረት ያጋጥማል የሚል ስጋት ሊኖር እንደማይችል በቅርቡ አስታውቋል ። ይሁንና ፋኦና ሌሎች ሮም የሚገኙ የምግብ ድርጅቶች የምግብ ዋስትና አሁንም አስተማማኝ አይደለም ሲሉ ማሳሰብ ላይ ናቸው ።

ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ፣ ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ