1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የምግብ ዋስትና መዘርዝርና ኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2004

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኝባቸው ሃገራት አንዷ መሆኗን ትናንት ይፋ የሆነ ዘገባ አመልክቷል ። ይሁንና በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተዘረጉት አሰራሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን

https://p.dw.com/p/15VMX
Safia Fungie Hasenna in her field in Adamitullu Jiddo Kombolcha district in Ethiopia. A combination of environmental degradation, prolonged drought and bursts of heavy rain has decimated her cattle and her crops. Credit: Zeresenay Berhane Mehar http://www.flickr.com/photos/oxfam/3969419136/ +++CC / Oxfam International+++ am 19.09.2009 aufgenommen im april 2011 geladen Lizenz:http://creativecommons.org/licenses/by-nc-nd/2.0/deed.de
ምስል CC / Oxfam International

የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ዴታ አስታውቀዋል ። ሚኒስትር ዴታ ምትኩ ካሳ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት አሰራሮች አንዱ የ Safety net ወይምየምግብለሥራመርሃግብርነው።ያምሆኖኢትዮጵያበጥር2004 ይፋእንዳደረገችውከህዝብዋ3.2 ሚሊዮኑየምግብእርዳታጠባቂ ናቸው

ትናንትይፋበሆነውየዓለምየምግብዋስትናመዘርዝርመሰረትከሰሃራበስተደቡብያሉየ 4 የአፍሪቃሃገራትየምግብዋስትናከዓለምበዝቅተኛደረጃላይይገኛል።እነርሱምኢትዮጵያሩዋንዳናይጀሪያናሞዛምቢክናቸው።ኢትዮጵያ ጥናቱ ከተካሄደባቸው 105 አገሮች በምግብ ዋስትና 100 ኛ ደረጃ ነው የተሰጣት ። በመዘርዝሩ ኢትዮጵያ ያገኘችውን ደረጃ መነሻ በማድረግ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ዴታ አቶ ምትኩ ካሳ በሰጡት አስተያየት የሃገሪቱ የምግብ ዋስትና ዝቅተኛ መሆኑ እንደሚታወቅ ገልፀው ሆኖም ሃገሪቱ ባወጣቻቸው እቅዶች መሰረት ውጤቶች መገኘታቸውን አብራርተዋል።

Ethiopian girl fetches drinking water
ምስል picture-alliance/Ton Koene

ምንም እንኳን በምግብ ለሥራ መርሃ ግብር ታቅፈውየነበሩ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ ዋስትና ተረጋግጧል ቢባልም ፤ ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ዘንድሮም የምግብ እርዳታ ተቀባይ ናቸው ።በአብዛኛው በዝናብ ላይ ጥገኛ በሆነው የኢትዮጵያ ግብርና በዓመት ውስጥ የሚጥለው ዝናብ በአጠቃላዩ ምርት መጠንና በምግብ ዋስትና ላይም ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ። ዘንድሮ እንደ ሶማሊያ ባሉ ጎረቤት ሃገራት የዝናብ እጥረት የምግብ ችግር አሰከትሏል ። ኢትዮጵያስ ይህ ያሰጋት ይሆን ? አቶ ምትኩ

View of the Awash river with Afar settlement in the distance , Assaita, Afar region, Ethiopia (via Ariadne Van Zandbergen/Africa Imagery/africanpictures.net)
ምስል picture-alliance / africamediaonline

ዋናጽህፈትቤቶቹለንደንኒውዮርክናሆንኮግየሚገኙትEconomist Intelegence Unit የተባለውየምጣኔሃብትአጥኚቡድንየዓለም የምግብ ዋስትና መዘርዝሩንለማውጣትየተጠቀመባቸውመመዘኛዎችበየአገሮቹምግብየመግዛትአቅም፣የምግብመገኘትእንዲሁምየምግብጥራትናደህንነትናቸው።በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየናረ የሄደው የምግብ ዋጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ይነገራል ። ይህም በሃገሪቱ የምግብ ዋስትና ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ እንደማይቀር ይገመታል ። ሚኒስትር ዴታ ምትኩ ካሳ ግን ችግሮቹ ጊዜያዊ ናቸው ይላሉ ።

ሒሩት መለሠ

ሸዋዬ ለገሠ