የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነት የመለውጥ ሂደት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 11 2002ማስታወቂያ
ክፍል ፩-የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነት ገጽታ በተለይም ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ባስከተለው ችግር ከሥር-መሠረቱ እየተለወጠ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ የዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋማት የ IMF ና የዓለም ባንክ ሚናም ይገኝበታል። ለመሆኑ እነዚህ ተቋማት እንዴት? ለምን ዓላማና ለማንስ ጥቅም ተቋቋሙ? በሂደት ብዙዎች ሁኔታዎችም ተከስተዋል። ለምሳሌ የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የፖለቲካ ተጽዕኖ አንዱ ነበር። ሌሎች ሁኔታዎችም አሉ። ለነዚህና ለተያያዙ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በስኮትላንድ ዳንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ሕግ መምሕር የሆኑትን ዶር/ መላኩ ደስታን አነጋግረናል።
MM SL