የዓለም አቀፉ የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤትና አፍሪቃ
ሰኞ፣ ኅዳር 13 2008የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት፤ የፍርድ ቤቱን ደንብ ሥልጣንና ኃላፊነት የሚደነግገዉን የሮማ ሰነድ የተባለዉን የፍርድ ቤቱን መመስረቻ ሰነድ በተቀበሉ አባል አገሮች እንደ ጎርጎርዮሳዊዉ አቆጣጠር 2002 ዓ,ም የተቋቋመና ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን እንዲዳኝ ስልጣን የተሰጠዉ የፍትህ ተቋም ነዉ። የፍርድ ቤቱ መሰረታዉ ሰነድ የሆነዉ የሮማዉ ሰነድ በዓለም ዙርያ በሰባዊነት ላይ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎችን የዘር ማጥፋትንና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶችን በዓለም አቀፍ ወንጀለኝነት በመፍረድ እነዚን ወንጀሎች መንግሥታት በራሳቸዉ መመርመርና መዳኘት ካልቻሉ ወይም ካፈለጉ ፍርድ ቤቱ እንዲያጣራና ካልቻሉ ወይም ካልፈለጉ ፍርድ ቤቱ እንዲያጣራና እንዲያስችል ስልጣን ይሰጣል።
የዚህን ፍርድ ቤት ስልጣንና ኃላፊነት የሚደነግገዉን የሮማን ሰነድ የተቀበሉትም አገሮች የፍርድ ቤቱን የሚያስተዳድሩ ሲሆን፤ በየዓመቱ በሚያደርጉት ጉባዔም የፍርድ ቤቱን የሥራ ሂደት ይመረምራሉ፤ መመርያም ይሰጣሉ። ዘንድሮ ግን ጉባኤዉ ፍርድ ቤቱንና የአፍሪቃ መንግሥታት የተወዛገቡበትና እሰጣ ገባ የበዛበት እንደሆነ ነዉ፤ ከጉባኤዉ የወጡት ምንጮች የሚያስረዱት ። የዛሬው ዜና ማህደር፣ የዓለማቀፉን የወንጀል መዳኛ ፍርድ ቤትና የአፍሪቃ መንግሥታትን ዉዝግብ ፤ እንዲሁም የፍርድ ቤቱን እጣ ፈንታ በሚመለከት የባለሞያን አስተያየትን አካቶ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ያስቃኘናል።
ገበያዉ ንጉሴ
አርያም ተክሌ