1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ባንክ ጉባዔና የሚሠነዘረው ነቀፌታ፧

ረቡዕ፣ መስከረም 19 1997

በዚህ ሳምንት ማለቂያ ላይ፧ ዋሽንግተን ውስጥ፧ የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በሚያካሂዱት ዓመታዊ ጉባዔ፧ አያሌ የገንዘብ ሚንስትሮች፧ የኤኮኖሚ ጠበብትና የባንክ ኀላፊዎች ይሰበሰባሉ። የፀጥታው አያያዝ ከምንጊዜውም ይልቅ የጠበቀ እንደሚሆን ይነገር እንጂ፧ ዓለም-አቀፉን አጽናፋዊ የኤኮኖሚ ትሥሥር(ግሎባላይዜሽን) የሚቃወሙትን ሰልፈኞች ከነአካቴው መግታት መቻሉ አጠራጣሪ ነው። ዛሬና ነገ፧ የአዳጊ አገሮች የኤኮኖሚ ይዞታ፧ የተገመገመባ

https://p.dw.com/p/E0fL

��ውና የመጪውን ዓመት የኤኮኖሚ ሂደት የሚጠቁሙ ፪ ሰፋ ያሉ ጥናት ነክ ሰነዶች ይቀርባሉ።

ዘንድሮም፧ ፻፹፭ ቱ የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አባል አገሮች መልክተኞቻቸውን ወደ ዋሽንግተን ልከዋል። በዚያም እንደተለመደው፧ የአያሌ ጥናት ስብስቦች፧ የኤኮኖሚ ዕድገት ነክ ሂደት፧ በአጠቃላይ የዓለም ኤኮኖሚ፧ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፧ «የዓለም ልማት-ነክ ዘገባ« በተሰኘው የምርምር ውጤት በኩል ቀርቦ ይደመጣል። በዓለም ባንክ፧ አውሮፓ ነክ ሥራ አስኪያጅ Kurt Bayer እንዲህ ይላሉ፧O-ton(
«በዓለም የልማት ዘገባ፧ እንደሚመስለኝ፧ እጅግ ጠቃሚው ፧ ለአዳጊ አገሮች ይዞታ በጣም ጥሩ ምልክት ሰጪነቱ ነው። ምክንያቱም፧ በመልማት ላይ በሚገኙት አገሮች የኤኮኖሚ ዕድገቱ ደረጃ፧ አምና፧ ባማካዩ፧ ከሞላ ጎደል፧ ፮ ከመቶ እንደነበረ በማሳየቱና፧ ይህም ከ ፴ ዓመት ወዲህ እጅግ ከፍተኛው የዕድገት መጠን መሆኑ በመታወቁ ነው« ብለዋል።
ይሁንና የተጠቀሰው የዕድገት መጠን፧ ሁሉን አዳጊ አገሮች አይመለከትም። በላቲን አሜሪካ፧ ለምሳሌ ያህል፧ ብራዚል ከእስያም ቻይና፧ በልማት አወንታዊ ገጽ ይታይባቸዋል። በድህነት ላይ ያካሄዱት የትግል ዘመቻም ተሳክቶላቸዋል። ከሰሃራ ምድረበዳ በስተደቡብ በሚገኙት የአፍሪቃ አህጉር ግን፧ ራሳቸውን በሙስና የተበተቡ መንግሥታት ዘላቂነት ያለው ዕድገት ማሳየት አልቻሉም። የሚሰጥ የልማት እርዳታም ቢሆን መቅኖ እያጣ ነው የሚቀረው። በልማት ነኩ ዘገባ ያልተካተተ ምን ይሆን?
O-ton(
«በሚገባ መመርመርም ሆነ በጥልቅ ማየት ይገባል። ግምቶች እንደሚጠቁሙት፧ ሲሦው የልማት እርዳታ፧ መድረስ ከሚገባው ቦታ አይደርስም። አውሮፓ ውስጥ ወደ አልታወቀ የባንክ ሰነድ እየተዛወረ ነው ገንዘቡ ቀልጦ የሚቀረው።«
የዓለምን ባንክና ዓለምአቀፉን የገንዘብ ድርጅት የሚጻረሩት፧ በዛ ያሉ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶችና የዓለም አቀፉ አጽናፋዊ የኤኮኖሚ ትሥሥር ተቃዋሚዎች ፪ቱን ታዋቂ የገንዘብ ተቋማት በጥብቅ ነው የሚነቅፉት። Friends of the Earth የተሰኘው የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ነክ ድርጅት ፕሬዚዳንት Brent Blackwelder እንዲህ ይላሉ።
O-ton(
«የዓለም ባንክ፧ ፳ ከመቶ ፕሮዠዎቹን በሚታደስ የኃይል ምንጭ ላይ ለማዋል ቃል ገብቷል። ይሁንና የተፈጥሮ አካባቢ በካዮች ከሆኑ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት፧ የተፈጥሮ ጋዝ፧ እንዲሁም የድንጋይ ከሰል ከሚወጣባቸው የማዕደን ጉድጓዶች ራሱን ለማራቅ አልፈለገም። አሁን የተጠቀሱት የማዕድን ማውጫ ጉድጓዶች አያያዝም ነው፧ ሰብአዊ መብትን የሚያስረግጥ፧ ተፈጥሮን የሚደመስስ፧ የሚበክልና የጤና ጠንቅ የሚያስከትል። በዓለም ዙሪያ፧ የአየር ጠባይ እንዲለውጥና በሁሉም ቦታ፧ ድሆች ይበልጥ እንዲጎዱም ማድረጉ የታወቀ ነው«።
የኤኮኖሚ ሊቅ፧ ራጉራም ራጃን የሚያቀርቡት ዘገባ ፪ቱን የገንዘብ ድርጅቶች እጅግ የሚነቅፍ እንደሚሆን ይነገራል። የጀርመን የኤኮኖሚ ዕድገት፧ በጣም አነስተኛ ነው የሚሆነው። ከአንድ ተኩል ከመቶ በታች እንደማይሆን የሚጠበቀው የጀርመን ኤኮኖሚ ዕድገት በአውሮፓው ኅብረት፧ ወሳኝነት ያለው ነው። ኩርት ባየር አሁንም እንዲህ ይላሉ።
O-ton(Also in.......)
«በጀርመን ሀገር የግሉ ፍጆታ ባለፈው እ ጎ አ በ 2003 ዓ ም አንድ ከመቶ ብቻ ዕድገት ሲያሳይ፧ በዩ ኤስ አሜሪካ ከ ፬-፭ በመቶ ነው የመጠቀው። ይህም በአሜሪካ ገንዘብ ሥራ ላይ እንዲውል ሲገፋፋ፧ በጀርመን አያነቃቃም። ይህም፧ የሥራ አጦች ቁጥር እንዲንርና አሉታዊ ሂደቶች እንዲስፋፉ ሊያደርግ ይችላል። ሊገታ የሚችለው፧ አወንታዊ የሆነ እርምጃ ሲወሰድ፧ ምናልባትም ህዝቡ፧ በአከራካሪው የተሃድሶ መርኀ-ግብር ሳቢያ፧ የመንፈስ አለመረጋጋት የደረሰበትን ሁኔታ መለወጥ ሲቻል ነው«ብለዋል።
ለቀረጥ ከፋዩ ህዝብ የተሳካ ሂደት ሊያጋጥም የሚችለው፧ የዋሽንግተኑ ጉባዔ፧ ፖለቲከኞችና የገንዘብ ጠበብት በጋራ የሚመክሩበት፧ ሌሎች እንዴት ሊሳካላቸው እንደቻለ ከተመክሮአቻው ሐሳብ ማግኘት የሚቻልበት መድረክ ቢሆን ነበር።
አሁንም በዓለም ባንክ፧ ዋናው ሥራ አስኪያጅ፧ ኩርት ባየር፧....
(O-ton Wenn ich offen bin........)
በግልጽ ለመናገር፧ ዘንድሮ፧ ስብሰባዎቹ እንዲገቱ ማድረጉን ነበረ የምመርጠው። በዚህ ዓይነቱ አያያዝ አንገብጋቢም ሆኑ ማለፊያ ጉዳዮች አልተወሱምኗ! ጠቃሚ የሚሆኑት ጉዳዮች፧ በእርግጥ የ፪ዮሽ ቀጠሮና ውይይቶች፧ የሚንስትሮች የእርስ በርስ ምክክርና የራስን ተመክሮ ለሌሎች ማካፈልና የመሳሰሉት ናቸው« ነበረ ያሉት።