የዓለም ባንክ ድጋፍ ለኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ መስከረም 6 2008ማስታወቂያ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያበድር ነዉ።ባንኩ እንዳስታወቀዉ ገንዘቡ ኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት አዉታሮችን ለማስገንባት፤ ጤናን ለማስፋፋትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ለምታደርገዉ ጥረት የሚዉል ነዉ።ባንኩ ባወጣዉ መግለጪያ እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምዕተ-ዓመቱን ግቦች ገቢር በማድረጉ ረገድ አበረታች ዉጤት አስመዝግባለች።የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ