የዓለም ባንክ ዘገባ እና ትችቱ
ሐሙስ፣ ኅዳር 29 2009ማስታወቂያ
የዓለም ባንክ ለአምስተኛ ጊዜ ባወጣዉ ዘገባዉ አክሎም የባቡር መስመር ግንባታዎች ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ለጎረቤት ሃገራት የማቅረቡ እንቅስቃሴ የሀገሪቱን የዉጭ ንግድ አቅርቦት እንደሚያሻሽልም አመልክቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የሚኖሩ አንድ የመስኩ ጠቢብ ግን ዘገባዉ ጥቂት እዉነታን ብቻ ያገናዘበ ነዉ ሲሉ ይተቻሉ። የባቡር የኤልክትሪክ ኃይል እና የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታዎች በብዙ ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና ብድር መምጣታቸዉንም መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ