የዓለም ባንክ አዲስ ፕሬዚደንት መምረጡ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2004ማስታወቂያ
የዕጩነቱን ጥያቄ በተመለከተ ብዙ አሻሚ ሀሳቦች ቀርበው እንደነበር አይዘነጋም። በተለይ ናይጀሪያዊትዋ የገንዘብ ሚንስትር በአሜሪካዊው ተፎካካሪያቸው አንጻር የምጣኔ ሀብት ምሁር በመሆናቸው፡ በአፍሪቃዊነታቸውና በሴትነታቸው የተነሳ በዓለም ትልቁን የልማትና ብድር ሰጪ ድርጅት የሆነውን የዓለም ባንክ እንዲመሩ የፈለጉ ጥቂቶች አልነበሩም። ያም ሆኖ ግን ዩኤስ አሜሪካ የራሷን ዕጩ ማስመረጡ እንደተጠበቀው ተሳክቶላታል። እርግጥ፣ የናይጀርያዋ የገንዘብ ሚንስትር እና የቀድሞዋ የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ ፕሬዝደንት ሆነዉ ለተመረጡት ተፎካካሪያቸዉ ለጂም ዮንግ ኪም የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክት ቢያስተላልፉም፣ አቡጃ ላይ ባደረጉት ንግግራቸው የምርጫዉ ሂደት ግልጽ መሆንና ችሎታን ያመዛዘነ መሆን ነበረበት ሲሉ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል። እና በአዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ምርጫ ሂደት ዩኤስ አሜሪካ የዓለም ባንክ አባል ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት የተጠቀመችበት ዘዴ ወይም በአባላቱ ላይ ያሳረፈችባቸው ተፅዕኖ ነበር ወይ? ቀደም ሲል በምርጫው ሂደት ላይ በስልክ ያነጋገርኩትን የዋሽንግተኑን ወኪላችን አበበ ፈለቀን በመጀመሪያ ጠይቄው ነበር።
አበበ ፈለቀ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ