የዓለም ባንክና ጎስቋሎች
ዓርብ፣ ሚያዝያ 9 2007ማስታወቂያ
የዓለም ባንክ ድሆችን ለመርዳት ልማትን በመንደፍ ብልጽግና ን ለማስገኘት የኑዋሪዎቹንም ሰብአዊ መብትና ክብር ለመጠበቅ መንቀሳቀስ ዓላማው መሆኑን ቢገልጽም ከአፍሪቃና ከሌሎች አካባቢዎች የሚታዩትና የሚሰሙት ሁኔታዎች ፤ አንድ ጥናት እንደሚለው የተጋላቢጦሽ ሆኖ ተገኝቷል። ይህን ያሉት ከ 36 ሃገራት የተውጣጡ በርካታ ጋዜጠኞች ናቸው። ጋዜጠኞቹ፤ ያካሄዱት ጥናት ፤ የሰበሰቡት መረጃ የዓለም ባንክ ገንዘቡን አፍሶ፤ በያለበት የጀመረውን ፕሮጀክት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ችግር ላይ እንደሚጥል ማስረጃዎቻቸውን ይዘው ቀርበዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ