የዓለም ማህበራዊ መድረክ ውይይት22 ጥር 2001ዓርብ፣ ጥር 22 2001ዕውቀታችን ከትምህርት ቤት አለያም ከዩኒቨርሲቲ የተገኘ አይደለም። ከቀደሙ አባቶቻችን የተቀዳ እንጂ። ደናችንን፣ ጅረቶቻችንን እንንከባከባለን። ያም እንዴት እንደሆነ እናውቅበታለን። ከተፈጥሮ ጋር ተጣጥመን ነው የምንኖረው። ተፈጥሮን አናቃውስም። ሌሎች ህብረተሰቦች ያን ያደርጉ ይሆናል፤ እኛ ነባር የህንድ ጎሳዎች ግን አናደርገውም።https://p.dw.com/p/Gk7qየአማዞን ደንምስል APማስታወቂያሰሞኑን ቤሌም ብራዚል ውስጥ በተያዘው የዓለም ማህበራዊ መድረክ ውይይት ላይ ከላቲን አሜሪካ የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር አሜሪካውያንና ከተለያየ ቦታ የመጡ የነባር ነዋሪዎች ተወካዮች መገኘታቸው ታውቓል። በሰሜን ብራዚል የአማዞን ክልል በሚገኘው የውይይት ስፍራ የአህጉሪቱ ተወላጆች የተሰባሰቡትበአለም ላይ የተከሰተውን የምጣኔ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግ ነው ።