የዓለም ሙቀት መጨመርና ሰበቡ
ዓርብ፣ መስከረም 17 2006ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት የዓየር ንብረት ለውጥ አጥኚዎች ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው የዛሬ 6 ዓመት ባቀረበው ዘገባ ለዓለማችን ሙቀት መጨመር የሰው ልጅ ድርሻ 90 በመቶ ነው ሲል የዘገበውን አሁን ወደ 95 በመቶ ከፍ አድርጎታል ። ችግሩን ለመከላከልም መንግስታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱና እጎአ እስከ 2015 አንድ የጋራ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ቡድኑ ጠይቋል ። ዛሬ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ይፋ የተደረገው ይኽው ዘገባ ባለ 2 ሺህ ገፅ ሲሆን ለፖሊሲ አውጭዎች የተዘጋጀ ተጨማሪ 36 ገፅ ማጠቃለያም አለው ። ዘገባው የተቀመረው በ 257 ሳይንቲስቶች ነው ። ስለዚሁ ዘገባ ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘውን ወኪላችንን ቴዎድሮስ ምህረቱን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ጠይቄው ነበር ።
ቴዎድሮስ ምህረቱ
ሂሩት መለሰ