የዓለም ሕዝብ ቁጥር ይጨምራል፤የተመድ3 መጋቢት 2001ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2001የተመድ አሁን ያለዉ የሕዝብ ቁጥር በመጪዉ የአዉሮጳዉያኑ 2012ዓ,ም ሰባት ቢሊዮን እንደሚደርስ አስታወቀ። ቁጥሩ በክፍተኛ ደረጃ የሚጨምረዉም በተለይ በእስያና አፍሪቃ በሚገኙ አዳጊ አገራት እንደሚሆን ተገምቷል።https://p.dw.com/p/HAhMበታዳጊዉ ዓለም ታዳጊዎች ይበዛሉምስል Deutsche Stiftung Weltbevölkerung (DSW)ማስታወቂያበተመሳሳይም አሁን ያለዉ ስድስት ነጥብ ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር በ2050ዓ,ም ዘጠኝ ቢሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ድርጅቱ ግምቱን ይፋ አድርጓል። ለባለሙያዎች አሳሳቢዉ ነገር የሕዝብ ቁጥርና የምጣኔ ሃብት እድገት አለመመጣጠን ነዉ። በአዳጊ አገራት ቤተሰቦች የልጆቻቸዉን ቁጥር መመጠን ቢሹም ስልቱ አልተመቻቸም። የበለፀጉት አገራት ደግሞ ሴቶቻቸዉ እንዲወልዱ ያበረታታሉ፤ የሚወልዱ ጥቂት ሆኑ። SL/NM