1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ዜጎች በጀርመን

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2002

የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ጀርመን ለሚኖሩ ለአብዛኛዎቹ የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ መኖር አዳጋች በሆነባቸው ምክንያቶችና እና ችግሩን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኩራል ።

https://p.dw.com/p/LD6f
የኮሎኝ ከተማምስል dpa

ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ፌደራል ክፍላተ ሀገር ፣ ምዕራባዊው የኖርድ ራይን ቬስት ፋይልያ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር በህዝብ ብዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ። የዚህ ክፍለ ሀገር ህዝቡ ቁጥር አስራ ሰባት ሚሊዮን ይደርሳል ። ይኽው ክፍለ ሀገር ከሌሎቹ ክፍላተ ሀገር ጋር ሲነፃፀር የበርካታ የውጭ ዜጎች መኖሪያ ነው ። ከበርሊን ከሀምቡርግ እና ከሙንሽን ቀጥሎ በትልቅነት አራተኛውን ደረጃ ከምትይዘው ከኮሎኝ ከተማ ነዋሪ ሲሶው የውጭ ዜጋ ነው ። በዚህች ከተማ ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች አብዛኛዎቹ ከህብረተሰቡ ጋር ያልተቀራረቡ የተገለሉና በዝቅተኛ ስራዎችም የተሰማሩ ናቸው ። ይህን ለመለወጥም በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ስር የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርበው የሚኖሩበትን መንገድ የሚያመቻች ምክር ቤት ከተመሰረተ አምስት ዓመት ተቆጥሯል ። የዚህ ምክር ቤት አባላት የመጀመሪያው ምርጫ የዛሬ አምስት ዓመት በህዳር ወር የተደረገ ሲሆን ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ እ.ጎ.አ በ2010 መጀመሪያ ላይ ይካሄዳል ። በዚህ ምርጫ ከሚወዳደሩት ውስጥ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ጀርመናዊ የሆነው የኮሎኝ ከተማ ነዋሪ ወጣት እስጢፋኖስ ሳሙኤል አንዱ ነው ።