1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ሠራተኖች አያያዝ በባህረ ሰላጤው ሃገራት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 26 2008

የመካከለኛው ምሥራቅዋ ቃታር ከ100 ዓመት በፊት የምጣኔ ሀብትዋ መዘወሪያ የባሪያ ንግድ ነበር ። በዚያን ጊዜ ከ5 የሀገሪቱ ነዋሪዎች አንዱ ባሪያ ነበር ።በቃታር ርዕሰ ከተማ ዶሃ የሚገኝ አንድ ቤተ መዘክር ይህን የቀድሞ ታሪክ ይዘክራል።

https://p.dw.com/p/1JtJU
Katar Ausländische Bauarbeiter warten auf ihren Bus zurück zur Unterkunft in Doha
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

ታዲያ በርግጥ አሁን በቃታር የባሪያ ንግድ ቆሟልን ? ወይስ አሁን ሌላ ስም ተስጥቶታል ? እውነታው ይላል የዶቼቬለው ካርስተን ኩኽንቶፕ በዚያ የሚሠሩ የውጭ ዜጎች በሚተዳደሩበት ከፈላ በተባለው ስርዓት ለከባድ የጉልበት ሥራ እና ለባርነት ይዳረጋሉ ።
ዶሃ የሚገኘው የባርያ ንግድ መታሰቢያ ቤተ መዘክር የቃታርን የባሪያ ንግድ ታሪክ መዝግቦ ይዟል ።ይሁንና ቤተ መዘክሩ በጎርጎሮሳዊው 2022 ቃታር ለምታስተናግደው የዓለም እግር ኳስ ጨዋታ በሚገነቡ መሠረተ ልማቶች ውስጥ ስለሚሠሩ በመቶ ሺህዎች ስለሚቆጠሩ የውጭ ዜጋ የጉልበት ሠራተኞች ምንም አያሳይም ።ይህ ለምን እንደሆነ የቤተ መዘክሩ ሃላፊ ፋሃድ አል ቱርካይ ሲናገሩ ።
« እኛ በአንድ ሰው ላይ ጣትን ለመቀሰር ወይንም አወዛጋቢ ታሪክን ቆፍረን ማውጣት አንፈልግም።ከዚያ ይልቅ ወቅታዊ ስለሆነው እና ሁላችንንም ስለሚያሳስበን ስለዚህ ጉዳይ ግንዛቤን ማስጨብ ነው የምንፈልገው ። »
የውጭ ዜጎች ቃታር ለሥራ የሚሄዱትተገደው ሳይሆን በፈቃዳቸው ነው ።እዚያም ቀድሞ እንደሚደረገው እንደ ባሪያ አይሸጡም ። ይሁንና ከፈላ የሚባለው ስርዓት እያንዳንዱ የውጭ ዜጋ ሠራተኛ ፣ ከአሠሪው ወይም ሃላፊነት ወስዶ ካመጣው ግለሰብ እስፖንሰሩ ጋር የግድ እንዲቆራኝ ያደርጋል ። ሠራተኛው ከቃትር ለቆ መውጣት ቢፈልግ ወይም ደግሞ የባንክ ሂሳብ ለመክፈት፣ አለያም መንጃ ፈቃድ ለማውጣት አሠሪው ወይም እስፖንሰሩ መስማማት ይኖርበታል ። ከዚህ ሌላ የሚበድሏቸውን ክፉ እና ጨካኝ አሠሪዎች ጥለው መሄድ የሚፈልጉም ከሆነ ያመጧቸው ሰዎች ስምምነት የግድ አስፈላጊ ነው ። የዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ኦድሪ ጋውግህራን እንዳሉት ቃታር ውስጥ እነዚህ ሠራተኞች የሚኖሩበት ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ከግዳጅ ሥራ ጋር ይመሳሰላል ።
«ለመሄድ ከሞከሩ ብዙውን ጊዜ ፓስፖርታቸውን በያዙባቸው አሠሪዎቻቸው ይከለከላሉ ። ወይም ሀገራቸው እዳ ስላለባቸው መመለስ ይፈራሉ ። እናም እዳቸውን ሳይከፍሉ መሄድ ያስፈራቸዋል ።
በመጪው ታህሳስ አንድ አዲስ ህግ ሥራ ይውላል ። በዚህ ህግ የከፈላ ስርዓት በተለይ በሠራተኞች ግዴታዎች ላይ ማሻሻያ ይደረግበታል ተብሏል ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ቃታር በሌሎች መስኮች ወደ ፊት እየተራመደች ነው ይላል ። ድርጅቱ እንደሚለው ለውጥ ከታየባቸው ውስጥ ቤት የማግኘት እና የክፍያ ጉዳዮች ይገኙበታል ።በከፈላ ስርዓት የሚተዳደሩ ሌሎች የባህረ ሰላጤው ሃገራትም አሉ ። ከነዚህ አንዷ የተባበሩት አርብ ኤምሪቶች ናት ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ የሂዩመን ራይትስ ባልደረባ ኒኮላስ ማክ ጌሃን እዚያም እንቅስቃሴዎች አሉ ይላሉ ።
«በአረብ ኤምሬቶች በከፈላ ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል ። በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ሁኔታዎች ሠራተኞች አሠሪ እንዲቀይሩ የሚፈቅድ ህግ አውጥተዋል ።ይህ ለሠራተኞች መብት የሚሰጠው ህግ ለኤምሪቶች ብቻ ባይሆን ኖሮ ለአካባቢው ሃገራትም አንድ ትልቅ እርምጃ ወደፊት ማለት ነበር ። »
የባህረ ሰላጤው ሃገራት ከፈላን የማስቀረት ብቻ ሳይሆን የማሻሻልም ችግሮች አሉባቸው ። የሃገሪው ሰዎች ለረዥም ጊዜ አናሳዎች ሆነው ነው የቆዩት ። በቃታርም ሆነ በኤምሪቶች በጣም ትንሽ ናቸው ። እናም ከፈላን ማሠሪያ ልጓምን በእጃቸው የሚያደርጉበት መንገድ አድርገው ነው የሚያዩት ። በነርሱ ሃላፊነት ሰዎች እንዲመጡ የሚደረግበት ስርዓት በሀገራቸው የመጨረሻ ዋስትናቸው አድርገው ነው የሚቆጥሩት ።ይሁን እና አሁን ለውጦች መምጣት እንዳለባቸው ግንዛቤ አለ። ሆኖም በመብት ተሟጋቾች አባባል በባህረ ሰላጤው ሀገራት የለውጥ ሂደቱ በበቂ ፍጥነት እየተራመደ አይደለም ወደፊትም አልገፋም ። በሃገሪቱ በከፈላ ምክንያት ሠራተኞች እንደሚበደሉ ቢታወቅም እንደ ሂዩመን ራይትስ ዋቹ ማክጌኽን አገላለጽ አሁን የውጭ ዜጎች በሙሉ እንደ ባሪያ ነው የሚሠሩት ማለት ግን ስህተት ነው ።
«በአንዳንድ የተለዩ ሁኔታዎች ባርነት ሊኖር ይችላል ። ሆኖም በኤምሪቶች በሥራ የተሰማሩ የውጭ ዜጎች በሙሉ እንደ ባርያ ነው የሚሠሩት ማለት ግን ስህተት እና የተጋነነም ነው ። ይህ አይደለም የሚታየው »

Arbeiter Baustelle in Doha Katar sklavenähnliche Zustände
ምስል Karim Jaafar/AFP/Getty Images
Katar Doha Gastarbeiter aus Nepal
ምስል Getty Images/AFP/M. Naamani

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ