የዋሽንግተን ሃቫና አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ
ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2007ማስታወቂያ
አሁን በሃቫናም እንዲሁ በአሜሪካን ኤምባሲም እንደዋሽንግተኑ የኩባ ኤምባሲ በይፋ ተከፍቷል። የኩባ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ሮድሪገዝ ዋሽንግተን ብቅ ብለዉ ከአሜሪካዉ አቻቸዉ ጆን ኬሪ ጋ ይነጋገራሉ የሀገራቸዉ ሰንደቅ ዓላማም በአዲሱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሠረት በኤምባሲያቸዉ ላይ ሲዉለበለብ ያስተዉላሉ። ኬሪም በቀጣዩ ወር ወደሃቫና ይጓዛሉ። ኩባና አሜሪካ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየ ግንኙነታቸዉን ለማደስ እጅግም ሳይሰማ ዉስጥዉስጡን ሲያካሂዱት የቆዩት ድርድር ከዳር መድረሱ ከተሰማ ሰባት ወራት ተቆጥረዋል። ዉይይት ድርድሩ ልዩነቶቻቸዉን ፈትቶ ጨርሷል ባይባልም ዛሬ ደግሞ በይፋ አንዳቸዉ በሌላቸዉ ዋና ከተማ የሚገኝ ኤምባሲያቸዉን በመክፈት ግንኙነታቸዉን አድሰዉ ታይተዋል። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ የኩባና ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማሲያዊ ትስስር በይፋ ስልተጀመረበት ሁኔታ በስልክ አነጋግሬዋለሁ። ዛሬ ዋሽንግተን በሚገኘዉ የኩባ ኤምባሲ ስለተከናወነዉ መክብብ እንዲህ ገልጾልኛል፤
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ