1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ግዥ በጀርመን

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2005

ሄሊኮፕተሮቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ለታሰበው ተግባር አመቺ እንዳልሆኑና የጥራት ደረጃቸውም ከጊዜው ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳይደለ ዛሬ ታትሞ የወጣው ፍራንክፉርተር አልገማይነ የተባለው የጀርመን ጋዜጣ ዘግቧል ።

https://p.dw.com/p/19WP4
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ቶማስ ደሜዝየር ለጀርመን ባህር ኃይል አገልግሎት የሚውሉ ሄሊኮፕተሮችን ለመግዛት የደረሱበት ውሳኔ እያወዛገበ ነው ። ሄሊኮፕተሮቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ለታሰበው ተግባር አመቺ እንዳልሆኑና የጥራት ደረጃቸውም ከጊዜው ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳይደለ ዛሬ ታትሞ የወጣው ፍራንክፉርተር አልገማይነ የተባለው የጀርመን ጋዜጣ ዘግቧል ። በግዢው ጨረታም የሌሎች አገሮች የጦር መሣሪያ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ አላደረጉም ተብለውም ተወቅሰዋል ። ሚንስትሩ ወደሰባት መቶ ሚሊዮን ዩሮ ገደማ አስወጥቶ ሃሳቡ አሁን ዉድቅ በሆነው አብራሪ የለሽ ዩሮ ሆክ በተሰኘዉ የጦር አዉሮፕላን ፕሮጀክት ከጥቂት ወራት ወዲህ የገጠማቸውም እክል ገና እልባት አላገኘም። በዚህም የተነሳ ተቃዋሚዎች ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ እየጠየቁ ነው ። ይልማ ኅይለ ሚካኤል ከበርሊን ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ