የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ እና የከንቲባው ምላሽ
ሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2007ማስታወቂያ
እርምጃው የማረራቸው አርሶ አደሮች ከከተማው መስተዳድር ለችግራቸው መፍትሄ እንዳላገኙ ም የዓይን ምስክሩ ተናግረዋል ።
የአይን ምስክሩ ለስራ ጉዳይ ወደ ወላይታ ሶዶ በሄዱበት አጋጣሚ አየሁ እንዳሉት በወላይታ ሶዶ ከተማ መስፋፋት ሰበብ ቤቶች የፈረሱትና አርሶ አደሮችም ከይዞታቸው የተፈናቀሉት በ8 የገበሪ ቀበሌማህበራት ነው ።
በነዚህ የገበሬ ቀበሌ ማህበራት ከሁለት ሳምንት በፊት በተጀመረው በዚሁ ዘመቻ የፈረ ሱት ከዓመታት በፊት እንዲሁም በቅርቡ ሃላፊዎች በፈቀዱት መሠረት ጭምር ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶች ናቸው ።
የዓይን ምስክሩ እንዳሉት ከነሐሴ አጋማሽ አንስቶ በቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ከ2500 በላይ ሰዎች መኖሪያ የነበሩ ቤቶች እንዲነሱ ተደርጓል ።በዚህ የተነሳም ብዙዎች መግቢያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው እንደ ዓይን ምስክሩ ።
ለከተማው መስተዳደር ሮሮአቸውን ያሰሙት ከይዞታቸው የተነሱት የወላይታ ሶዶ አካባቢ አርሶ አደሮች ለችግራቸውም ሆነ ለስጋታቸው መፍትሄ የሚሆን መልስ አላገኙም ። በዚህ የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ ላይ ከንቲባው ምላሽ ሰጥተውናል።
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ
አዜብ ታደሰ