1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወላይታ መስተዳድር የምርጫ ዉዝግብ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7 2007

ከስምንቱ ፓርቲዎች ቢያንስ የሁለቱ (የመድረክና የአንድነት) ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ዕጩዎቹ ከዉድድሩ ለመዉጣት አስጠንቅቀዋል ሥለመባሉ የሚያዉቁት ነገር የለም።የአንድነት ፓርቲ ከዚሕም አልፈዉ ወንጀል ተፈፅሟል ባይ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/1F90Y
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW

በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ-መስተዳድር በመጪዉ ግንቦት ለሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች፤ከየፓርቲዎቻቸዉ፤ ፓርቲዎቹ ደግሞ አንዳቸዉ ከሌላቸዉ ጋር እየተወዛገቡ ነዉ።የሰማያዊ ፓርቲ ባለሥልጣናት የራሳቸዉን ፓርቲ ጨምሮ የስምንት ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች በደረሰባቸዉ ጫና እና ወከባ ምክንያት እራሳቸዉን ከዉድድር እንደሚያገሉ ማስጠንቀቃቸዉን አስታዉቆ ነበረ።ከስምንቱ ፓርቲዎች ቢያንስ የሁለቱ (የመድረክና የአንድነት)ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ዕጩዎቹ ከዉድድሩ ለመዉጣት አስጠንቅቀዋል ሥለመባሉ የሚያዉቁት ነገር የለም።የአንድነት ፓርቲ ከዚሕም አልፈዉ ወንጀል ተፈፅሟል ባይ ናቸዉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ