1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወለኔ ፓርቲ መሪዎች ተለቀቁ

ረቡዕ፣ ኅዳር 18 2006

ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሱ ሌሎች የፓርቲዉ ባለሥልጣናት አሁንም እንደታሠሩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ያነጋገራቸዉ የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር እንዳስታወቁት የሕዝባቸዉ መብት እንዲከበር የጀመሩትን ትግል ከእንግዲሕም ይቀጥላሉ።

https://p.dw.com/p/1APb3
Titel Wolene peoples democratic party leaders Schlagworte Äthiopien, Wolene ,Addis Abeba Datum 271113 Fotograf Getachew Tedla Hailegiorgis
ምስል DW/G.T. Hailegiorgis

የወለኔ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪዎች ከዓንድ ዓመት በላይ ከታሰሩ በሕዋላ ሰሞኑን በነፃ ተለቅቀዋል።የፓርቲዉ መሪዎች ከእስር ከተፈቱ በሕዋላ አዲስ አበባ እንዳሳታወቁት ካአንድ ዓመት በላይ ለእስራት የተዳረጉት በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የተረጋገጠዉ የወለኔ ሕዝብ ማንነትና መብት እንዲከበር በመጠየቃቸዉ ነዉ።ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሱ ሌሎች የፓርቲዉ ባለሥልጣናት አሁንም እንደታሠሩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ያነጋገራቸዉ የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር እንዳስታወቁት የሕዝባቸዉ መብት እንዲከበር የጀመሩትን ትግል ከእንግዲሕም ይቀጥላሉ።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ