የኮፐንሐገኑ ጉባኤና አፍሪቃ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 8 2002ማስታወቂያ
በያዝነዉ ወር ማብቂያ ኮፐንሐገን-ዴንማርክ የሚሰየመዉ አለም አቀፍ የአየር ንብረት የመሪዎች ጉባኤ የአለምን የሙቀት ልቀት መጠንን በአስር-አመት ዉስጥ በግማሽ የሚቀንስ ዉሳኔ እንዲያሳልፍ አፍሪቃ ጠየቀች።በጉባኤዉ ላይ አፍሪቃን ወክሎ የሚሳተፈዉ ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀዉ አፍሪቃ ያለ ጥፋቷ ለደረሰባት የአየር ብክለት ጉዳትም የመቶ ቢሊዮን ዶላር ካሳ ትጠይቃለች።አፍሪቃን የሚወክሉት የአስር ሐገራት መሪዎችና ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተሰብስበዉ የመጨረሻ ባሏቸዉ ሐሳቦች ላይ መክረዋል።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝሩን ልኮል ናል።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ