1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮፐንሃገኑ የአየር ጠባይ ድርድር

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2001

በአዉሮጳዉያኑ 2012ዓም የሚያበቃዉን የኪዮቶ ዉል በመባል የሚታወቀዉን የአካባቢ ጥበቃ ህግ ለመተካት የሚያስችል ዉል ለመቅረፅ ጥረቱ ቀጥሏል። ሰሞኑን በየደረጀዉና በተለያዩ አገራት የአየር ጠባይ ለዉጥን ለመታደግ ዓለም ሊያደርግ የሚገባዉን ጥረት በሚመለከትም ጉባኤዎች እየተካሄዱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/Hxn9
አል ጎር በኮፐንሃገንምስል AP

ተስፋ ለበራዎች

የጃፓን ሳይንቲስቶች በአይጦች ላይ ባካሄዱት ምርምር ገና በወጣትነት እድሜ ክልል ሳሉ ለጸጉር መመለጥ ወይም በራነት የሚዳርገዉን ምክንያት ደርሱበት። የዚህ ጂን ማለትም ዘረመል ምንነት መገኘትም እድሜ ሳይገፋ ጸጉር እንዳይመለጥ መከላከል የሚያስችል መፍትሄ ለማግኘት እንደሚረዳቸዉ ተገምቷል። የተመራማሪዎቹ ቡድን ያገኘዉ Sox21 የተሰኘዉ ዘረመል ሰዎችም አይጦችም ላይ የሚገኝ ሲሆን በአግባቡ አለመስራቱ እድሜ ሳይደርስ ጸጉርን ለማጣት ይዳርጋል ነዉ ያሉት። አይጦችን በተወለዱ በ15ቀናቸዉ ጀምረዉ ዘረመሉ በሰዉነታቸዉ እንዳይሰራ አግደዉ ተመራማሪዎቹ እንዳስተዋሉት በሳምንት ዉስጥ መርገፍ የጀመረዉ ጸጉራቸዉ ጨርሶ ተመልጧል። በጃፓን ብሄራዊ የስነተፈጥሮ ተቋም በአጥቢዎች ዙሪያ በሚመራመረዉ ዘርፍ ፕሮፌሰር የሆኑት ዩሚኮ ሳጋ እንደሚሉት በሌላ ምክንያት የሚረግፍ ጸጉር ተመልሶ ሊበቅል የሚችልበት አጋጣሚ እጅግ ሰፊ ቢሆን የእነዚህ አይጦች ግን ሊመለስ አልተቻለም። Sox21 የተባለዉ ጂን ወይም ዘረመል ቀደም ሲል ይታወቅ የነበረዉ የነርቭ ሴሎችን በመፍጠሩ ሲሆን አሁን የጃፓኖቹ ጥናት ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገዉ ጸጉርም ያለጊዜዉ እንዳይረግፍ መርዳት መቻሉንም ነዉ። ሌላዉ ቀርቶ ጉድለቱ ጸጉር እንዲሳሳም እንደሚደርግ ነዉ ባለሙያዋ የተናገሩት። ይህ መታወቁም ወደመፍትሄዉ ያቀርበናል የሚል ተስፋም አላቸዉ። እንግዲህ ለበራዎችና ለሚያሰጋቸዉ ሁሉ መልካም ዜና ይመስላል።

ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ