የኮንጎ ግጭት፥ የሶማሊያ ጦርነት እና የዳርፉር ሠላም
ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2001ማስታወቂያ
የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግሥት ጦርነ በመንግሥት ላይ ያመፁት ጄኔራል ሎራ ንኩንዳ የሚመሯቸዉ ሸማቂዎች ምሥራቃዊ ኮንጎ አዲስ የጀመሩት ዉጊያ የሚቆምበት ብልሐት አለምን ሲያነጋግር፥ የጀርመን ፖሊስ አንዲት የሩዋንዳ ባለሥልጣን ማሰሩ የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት አሻክሮታል።የሶማሊያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የፈረሙት የሰላም ዉል ገቢራዊ የሚሆንበት ቀን ሲናፈቅ አል-ሽባብ የተባለዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ርዕሠ-ከተማ መቅዲሾን ለመቆጣጠር መገሥገሱ ተስምቷል።በዚሕ መሐል ነዉ-የሱዳኑ ፕሬዝዳት ዑመር ሐሰን አል-በሽር ዳርፉር የሚዋጋ ጦራቸዉ ተኩስ እንደሚያቆም ያወጁት።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።እሁለት የሚከፈለዉ ትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅታችን የአፍሪቃን መሰንበቻ ይቃኛል አብራችሁኝ ቆዩ።